የአሁኑ ቋንቋ: am ኣማርኛ

ቋንቋ
Selected Language:

አስተማሪ

በደፋርነቱና በጋለ ተነሣሽነቱ የሚታወቀው ጆን ቢቭሬ Extraordinary, የሰይጣን ሽንገላ, The Fear of the Lord, Under Cover, እና Driven by Eternity የተሰኙትና ሌሎች ከፍተኛ ተነባቢነት ያላቸው መጻሕፍት ደራሲ ነው። መጻሕፍቶቹ ከ100 በላይ ቋንቋዎች ተተረጒመዋል ‹‹ዘ ሜሴንጀር›› የተሰኘው ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በዓለም ዙሪያ እየተሰራጨ ነው፡፡ ጆን በየኮንፈረንሱና በየአብያተ ክርስቲያናቱ ታዋቂ ሰባኪ ነው፤ የእግዚአብሔርን መርሖዎች መረዳትና ተግባር ላይ ማዋል ለሚፈልጉ ሁሉ አገልግሎቱ ሕይወት ለዋጭ መልእክቶች ያቀርባል፡፡ ጆን እንደ እርሱ ከፍተኛ ተነባቢ ከሆነችው ሚስቱ ሊዛ ጋር፣ እንዲሁም ከአራት ወንዶች ልጆቻቸው፣ ከምራታቸውና የልጅ ልጆቻቸው ጋር በኮሎራዶ ስፕሪንግስ ኮሎራዶ ይኖራሉ፡፡

ማውረድ የሚቻሉ ነገሮች ተመልከት ኢ-ሜል ጆን ቢቭሬ

ተነሳሽነት ያላት፣ ለፍትሕ ተቆርቋሪ፣ ደፋር፣ ባለ ራእይና ጨዋታ ዐዋቂ የተሰኙት ቃላት ሊዛ ቢቭሬን ይገልጿታል፡፡ ሊዛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ንግግር የምታደርግና የተወዳጅ መጻሕፍት ደራሲ ስትሆን ከባልዋ ጋር በመሆን፣ ከ200 አገሮች በላይ የሚሰራጨው ሜሴንጀር የተሰኘውን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ታዘጋጃለች፡፡ በጣም ግልጽ በሆነ አቀራረብ ሊዛ ለሰዎች ሕይወት፣ ነጻነትና ለውጥ የሚያመጣውን የእግዚአብሔርን ቃል ከግል ሕይወት ልምምዷ ጋር እያዋዛች ታቀርባለች፡፡ እንደ አንድ የፍትሕ መስፈን ተቆርቋሪ አስከፊ ለሆኑ ሁኔታዎች ሌሎችም መልስ እንዲሆኑ በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉትን ታነሣሣለች፡፡ ከትዳር ጋደኛዋ ጆን ቢቭሬ፣ ከአራት ወንዶች ልጆቻቸውና ከልጃቸው ሚስትና ደስ ከሚሉ የልጅ ልጆቻቸው ጋር ጊዜ ማሳለፍን ትወዳለች፡፡

ማውረድ የሚቻሉ ነገሮች ተመልከት ኢ-ሜል ሊዛ ቢቭሬ