መነሻ ገጽ - ቪድዮዎች - ከመሸፈኛው ሥር ቪዲዮ መልእክት

 
ከመሸፈኛው ሥር ቪዲዮ መልእክት
ከመሸፈኛው ሥር ቪዲዮ መልእክት
አስተማሪ: ጆን ቢቭሬ

ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ነጻነት፣ ልግስና እና ጥበቃ አለ፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ግን ብዙዎች እንዴት ይህን ምስጢር ቦታ ማግኘት እንደሚችሉ አልተረዱም፡፡ ይልቁንም፣ እውነተኛና ዘላቂ ነጻነት ከመለኮታዊ ሥልጣን ውጪ እንደሚገኝ ለማመን ተታልለዋል፡፡

ከመሸፈኛው ሥር በተሰኘ መልእክቱ መለኮታዊ ሥልጣንን እንዳንገነዘብና በተገቢ መልኩ ከዚያ ጋር እንዳንያያዝ ለማድረግ ጠላት የሚጠቀምበትን የረቀቀና አደገኛ ዘዴ ያጋልጣል፡፡ ከተግባራዊ ምሳሌዎችና ጠንካራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ጋር ይህ መልእክት የእግዚአብሔር መንግሥት፣ በሥርዓትና በሥልጣን የሚመራ፣ በንጉሥ የሚተዳደር መንግሥት መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡

የእግዚአብሔርን ቃል እውነት ስትቀበል ለሚደርስብህ በጐም ሆነ ክፉ ነገር እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለብህ ትማራለህ፡፡ በእውነተኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መገዛትና መታዘዝ መካከል ያለውን ልዩነት ትረዳለህ፤ ሥልጣንን አስመልክቶ እግዚአብሔር ስላለው ዓላማ ትረዳለህ፡፡ ይህ መልእክት በሙላትና በእግዚአብሔር ባሕርያት መሠረት መመላለስ ወደምትችልበት ደረጃ ከፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ማጋራት