መነሻ ገጽ - መጻሕፍት - ጽናት መጽሐፍ

ጽናት መጽሐፍ
አስተማሪ: ጆን ቢቭሬ

የተለያዩ ችግሮች ይደርሱብሃል፡፡ ከባድ ሁኔታዎችን በጽናት መቀበል ታውቃለህ፡፡ አሸንፈህ እንደምትወጣ ተስፋ በማድረግ በጽናት ትታገላለህ፣ ትጥቅህን ታጠብቃለህ፣ የመጥፎ አጋጣሚዎችን ወጀብ ትታገላለህ፡፡

ግን፣ እነዚህ ችግሮች ሕይወትህን የመለወጥ ዐቅም ያላቸው ቢሆኑስ? እየተጋፈጥህ ያለው ችግር ለሚከተለው የእምነትና የብስለት ደረጃ የሚያነሣሣህ ቢሆንስ? ለአንተ የታሰበው ችግሩን ዘልቀህ እንድትወጣ ብቻ ሳይሆን፣ በዚያ ውስጥ እንድታድግ ቢሆንስ?

ጽናት በተሰኘው መጽሐፉ ጆን ቢቭሬ ጸንተህ ለመኖር በሚያስችልህ መንገድ ሊመራህ ይፈልጋል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስና በዘመኑ ካሉ ሰዎች ሕይወት በሚያቀርበው ታሪክ፣ እነዚህ ወንዶችና ሴቶች የእምነት ሰዎች በችግር ውስጥ ማለፍ ብቻ ሳይሆን፣ ችግርን ፊት ለፊት ተቋቁመው ማሸነፋቸውን ያመለክታል፡፡

በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት ኃይል በመታጠቅ ፈተናንና ተቃውሞን፣ እንዲሁም በሕይወትህ የእግዚአብሔር ዓላማ መፈጸሙን አስመልክቶ ሕይወት ለዋጭ እውነት ትረዳለህ፡፡ በእምነት ከእግዚአብሔር የተወለድህ እንደ መሆንህ መጠን፣ ችግርን ወደ ብርታት ለመለወጥና የጀመርከውን በሚገባ ለመፈጸም የሚያስችለው ነገር ሁሉ አለህ!

ሌሎች ሀብቶች
ጽናት የጥናት መመሪያ እና በጽሞና ማሰላሰያ
ጽናት ትምህርት በቪድዮ
ጽናት ትምህርት በድምፅ
ጽናት ትምህርት በንባብ

አውርድ (~6.9 MB)

ማጋራት