መነሻ ገጽ - መጻሕፍት - እንስት አንበሶቹ ይነሣሉ

እንስት አንበሶቹ ይነሣሉ
አስተማሪ: ሊዛ ቢቭሬ

የእንስት አንበሳዋ ከእንቅልፏ መንቃት የብርታት፣ የጋለ ተነሣሽነትና የውበት ድንቅ ምሳሌ ነው፡፡ በቦታው መገኘቷ ብቻ አካባቢን ያረጋጋል፣ ግልገሎቿን ይጠብቃል፣ ለባልዋ ሞገስ ይሆናል፡፡ በተለይ ደግሞ በቡድኑ ሲሆኑ እንስት አንበሶቹ በዙሪያቸው ያለውን ሁኔታ ለመለወጥ እንደ አንድ ሆነው ይንቀሳቀሳሉ፡፡

እንስት አንበሳ ነሽ

እንስት አንበሶቹ ይነሣሉ በሚለው መጽሐፍ ሊዛ ቢቭሬ ቁጡና ርኅሩኅ የሆነው የእንስት አንበሳ ሕይወትና ምሳሌ ለሴቶች አርዓያነት እንዳለው ታመለክታለች፡፡ የዚህችን አስገራሚ ፍጡር አስደናቂ ባሕርያት በመዘርዘር እርስ በርስ እንዲተሳሰቡ፣ በዓላማ እንዲያገለግሉና በጸሎት እንዲደፍሩ ሊዛ ሴቶችን ታበረታታለች፡፡ በዚህ መልእክት አማካይነት እንዴት ልጆቻችሁን እንደምትጠብቁና ድምፅ ለሌላቸው ወገኖች እንዴት ድምፃችሁን እንምታሰሙ ትረዳላችሁ፡፡

ከተፈጥሮና ከጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በመነሣት አስደማሚ ዕይታዎች የሚያቀርበው ይህ እንስት አንበሶቹ ይነሣሉ የተሰኘው መጽሐፍ፣ በምድር ላይ መልካም ለውጥ የሚያመጡ አንድ ስልታዊ ኃይል ሆነው እንዲሰባሰቡ ለሴቶች ሁሉ የቀረበ ጥሪ ነው፡፡

ከዚህ ሁሉ በላይ ክርስቶስ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ ተብሎ መጠራቱን አትርሱ፡፡ እኛ ደግሞ ከእንቅልፍ እየተነሡ ያሉ አንበሶቹ ነን፡፡

አውርድ (~2.6 MB)

ማጋራት