የአሁኑ ቋንቋ: am ኣማርኛ

ቋንቋ

መነሻ ገጽ - መጻሕፍት - እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዴት ነው ያለኸው?!

እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዴት ነው ያለኸው?!
አስተማሪ: ጆን ቢቭሬ
የሚገኝባቸው ቋንቋዎች:

በምድረ በዳ ጒዞህ የእግዚአብሔርን ብርታትና ዓላማ በሕይወትህ መለማመድ

አዳጋችና አስቸጋሪ ወቅቶች ሲገጥሙህ ግራ በመጋባት፣ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዴት ነው ያለኸው?!›› በማለት እየጠየቅህ ይሆን?

ምናልባት በአንድ ወቅት እግዚአብሔር ተናግሮህ ይሆናል፤ አሁን ግን፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በፍጹም ድምፁን አጥፍቶብሃል፡፡ ምናልባትም፣ የምትችለውን ያህል በእምነት እየተንቀሳቀስህ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ፣ በፍጹም ሓልዎቱን መለማመድ አልቻልህም፡፡ አሁን ያለህበት ቦታ ወይም ሁኔታ ምድረ በዳ ሊሆን ይችላል፤ ምድረ በዳ የእግዚአብሔርን ተስፋ ቃል በመቀበልና ተስፋ ቃሉ ሲፈጸም በማየት መካከል ያለ ቦታ ነው፡፡

ግን፣ ደስ የሚያሰኝ ዜና አለ፤ አሁን ያለህበት ቦታ፣ ምንም ዓላማ የሌለውና ጠፍ ምድር አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ምድረ በዳውን እርሱ ላዘጋጀው ፍጻሜ አንተን ለማዘጋጀት ይጠቀምበታል፤ ያ የሚሆነው ግን በትክክል አቅጣጫ ይዘህ ከተጓዝህ ነው፡፡ ብዙዎች በስሕተት እንደሚሉት፣ ይህ ቦታ ወይም ወቅት እግዚአብሔርን በትዕግሥት የመጠበቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ አሁን ባለህበት ምድረ በዳ ውስጥ በድል ለማለፍ የአንተም ትልቅ ድርሻ ይኖራል፡፡ ወዲያ ወዲህ በመንከራተት ጊዜህ እንዳይባክን ከፈለግህ፣ የአንተ ድርሻ ምን እንደ ሆነ መረዳቱ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

በዚህ ዐይን ገላጭ መጽሐፍ፣ ከፍተኛ ተነባቢነት ያለው ደራሲ ጆን ቢቭሬ፣ በደረቅና አዳጋች ወቅቶች ውስጥ አልፈህ እግዚአብሔር ለአንተ ወዳዘጋጀው መግባት እንድትችል ሁነኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕይታዎችንና ትምህርት ሰጪ ታሪኮችን ያቀርብልሃል፡፡

ሌሎች ሀብቶች
እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዴት ነው ያለኸው?! ትምህርት በቪድዮ
እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዴት ነው ያለኸው?! ትምህርት በድምፅ
እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዴት ነው ያለኸው?! ትምህርት በንባብ

አውርድ (~3.43 MB)

ማጋራት