የአሁኑ ቋንቋ: am ኣማርኛ

ቋንቋ
Selected Language:

መነሻ ገጽ - መጻሕፍት - የሰይጣን ሽንገላ

የሰይጣን ሽንገላ
አስተማሪ: ጆን ቢቭሬ
የሚገኝባቸው ቋንቋዎች:

የሰይጣን ሽንገላ የተሰኘው መጽሐፍ አማኞችን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ለማስወጣት ጠላት የሚጠቀምበትን አንድ አደገኛ ማሳሳቻ ወጥመድ ያጋልጣል – ይኸውም መሰናከያ ነው፡፡ አብዛኞቹ ሰዎች በዚህ መሰናከያ ተጠምደዋል፤ ያም ሆኖ ግን መጠመዳቸውን እንኳ አላወቁም፡፡

አትሞኙ! ክርስቶስ ራሱ፣ ‹‹ሰዎችን የሚያሰናክል መምጣቱ አይቀርም›› ብሏል (ሉቃስ 17፥1)፡፡ ማሰናከያው እንዲመጣ ወይም እንዳይመጣ ማድረግ አትችልም፤ ማሰናከያው ሲመጣ ምን ምላሽ እንደምትሰጥ ግን መምረጥ ትችላለህ፡፡ ማሰናከያውን በተገቢ መንገድ ካስተናገድህ መራራ ከመሆን ይልቅ ብርቱ ትሆናለህ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያልተቋረጠ ግንኙነት እንዲኖርህ የሚያስችልህ የምትሰጠው ትክክለኛ ምላሽ ብቻ ነው፡፡

በዚህ መልእክት ጆን ቢቭሬ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ጸንተህ እንድትኖርና የጥርጥርንና ያለ ማመንን ወጥመድ ሰብረህ፣ ነጻ ለመውጣት የሚያበቃህን ኃይል ሊያሳይህ ይሞክራል፡፡ ተጠቂ ከመሆን ዝንባሌ አምልጠህ ከተስፋ መቁረጥና ይበልጥ እየባሰ ከሚሄድ ሸክም ነጻ ሆነህ መኖር ትችላለህ፡፡ ለእግዚአብሔር የመገዛትን የላቀ ደረጃ ስትረዳ፣ ሕይወትህ በይቅር ባይነት፣ በዕርቅና እያደገ በሚሄድ ደስታ ይሞላል፡፡

ሌሎች ሀብቶች
የሰይጣን ሽንገላ ትምህርት በቪድዮ
የሰይጣን ሽንገላ ትምህርት በድምፅ
የሰይጣን ሽንገላ ትምህርት በንባብ

አውርድ (~2 MB)

ማጋራት