የአሁኑ ቋንቋ: am ኣማርኛ

ቋንቋ
Selected Language:

መነሻ ገጽ - ስለ

Cloud Libraryን በተመለከተ

ያሉበትን ቦታ ወይም የኢኮኖሚ ሁኔታ ግምት ውስጥ ሳያስገባ፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና መጋቢዎች እነዚህን አጋዥ ምንጮች ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ሜሴንጀር ኢንተርናሽናል ትኩረቱን መላው ዓለም ላይ አድርጓል፡፡ Cloud Library የተመሠረተው ለዚሁ ዓላማ ነው፡፡ የተተረጐሙ መጻሕፍትና አጋዥ መረጃዎች በነጻ እንዲሠራጩና እንዲወርዱ (download) ዓለም አቀፍ የስርጭት ማዕከል በመሆን ያገለግላል፡፡

ግባችን እነዚህ አጋዥ ምንጮች በማንኛውም አገር ዋና ቋንቋ እንዲገኙ ማስቻል በመሆኑ 98% የሚሆነውን የዓለም ሕዝብ የምንደርስበት ዐቅም ማጠናከር ነው፡፡ Cloud Library ይህን ግብ የምናሳካበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ እንዴት? ብላችሁ ብትጠይቁ መልሳችን በኢንተርኔት የሚሰራጩ ነገሮች ከቁሳዊ ነገሮች የበለጠ በፍጥነት መባዛትና መጓዝ ስለሚችሉ የሚል ይሆናል፡፡ አንተም ብትሆን በክላውድ ላይብሬሪ በሚኖርህ ልምምድ ደስተኛ እንደምትሆን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ከአዘጋጆቹ

ኢየሱስ የሰጠን ኃላፊነት ወንጌልን እንድሰብክ ብቻ ሳይሆን ደቀመዛሙርት እንድናደርግ ጭምር ነው፡፡ እነዚህ መልእክቶች የክርስቶስ ደቀመዝሙር ለመሆን ይረዱሃል፡፡ በእግዚአብሔር ጸጋ ሌሎችም ላይ በጐ ተፅዕኖ ለማድረግ ባለህ ችሎታ ስለምንተማመን ለአንተ ተገቢ ሥልጠና ለመስጠት የዐቅማችንን እናደርጋለን፡፡ አንተ ውስጥ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አኑሮአል፤ የበለጠ ከአንተ ጋር መቀራረብም ይፈልጋል፡፡ እነዚህ ጽሑፎችና አጋዥ ምንጮች፣ ከእግዚአብሔር ጋር የበለጠ ጥብቅ ግንኙነት ለማድረግ ይረዱሃል፡፡ ከክርስቶስ ጋር ባለህ ግንኙነት ስታድግ በቃሉ ኃይል ለዘለቄታው ትለወጣለህ፡፡

እግዚአብሔር ለተለየ ዓላማ ፈጥሮሃል፤ በተሰጡህ ስጦታዎች አማካይነት ሌሎች ላይ መልካም የሆነ ተፅዕኖ እንድታደርግም ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ለአንተ ያለውን ማንኛውንም ነገር እንድፈልግና በሙላት መረዳት እንድትችል እናበረታታሃለን፡፡ በምታደርገው ፍለጋ እነዚህ አጋዥ ምንጮች የበለጠ እንዲያዘጋጁህ ጸሎታችን ነው፡፡

እግዚአብሔር አንተንና የአንተ የሆነውን ሁሉ ይባርክ

ጆን እና ሊዛ ቢቭሬ

ለመርዳት ራእይ ካለህ

እነዚህ ሕይወት – ለዋጭ ምንጮች በዓለም ሁሉ እንዲዳረሱ ለመርዳት ልብህ ይቀጣጠላል? የክላውድ ላይብሬሪን (Cloud Library) ተልዕኮ የመርዳት ፍላጐት ካለህ፣ እባክህ ለ getinvolved@cloudlibrary.org email አድርግ፡፡ ለጸሎትህና ለምታደርገው ርዳታ በቅድሚያ እናመሰግናለን!